Returning to Ethiopia (Amharic, accessible)
Updated 15 September 2026
ምን አይነት እገዛ ተደርጎሎዎታል?
ከጉዞ በፊት የሚሰጥ መረጃ
ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች IRARAን በማነጋገር ወደ ኢትዮጵያ የመቀላቀል አማራጮችን መወያየት ይችላሉ።
የአጭር ጊዜ ወይም ጊዜያዊ ድጋፍ
-
የአየር ማረፊያ አቀባበል (ጥያቄው ሲቀርብ)
-
እስከ አምስት ሌሊት ማርፊያ
-
በአገር ውስጥ ወደሚገኝ መዳረሻ መጓጓዣ
-
የእንክብካቤ እና የምግብ አቅርቦት ፓኬጆች
-
ለአስቸኳይ ፍላጎቶች የሚሆን አነስተኛ የገንዘብ ድጋፍ
አገልግሎቶች የሚገኙት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ብቻ ነው።
የመካከለኛ ጊዜ ድጋፍ
- ቤተሰብን ለማፈላለግ እና ከቤተሰብ ጋር የማገናኘት እገዛ
- በአገር ውስጥ ሰነዶችን ለማሟላት የሚረዳ ድጋፍ
- የአካባቢ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማገናኘት ወይም ማመላከት
- የአእምሮ ደህንነት እና ምክር አገልግሎት (አስፈላጊ ከሆነ)
የረጅም ጊዜ ወይም ዘለቄታዊ ድጋፎች
ከስደት ተመላሾች የትምህርት እና የስራ መፍጠሪያ ፈንድ ማመቻቸት
- በህጋዊ ስደተኝነት እድሎች/አማራጮች ላይ የሚደረግ ድጋፍ
- የአካባቢው የሥራ ገበያ በመድረስ ላይ ድጋፍ መሰጠት
- በንግድ የስራ ዘርፍ የማቋቋም ድጋፍ
- የሙያ ስልጠና ወይም ተጨማሪ ትምህርት የማግኘት ድጋፍ
ማን ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል?
ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመለሱ ወይም የሚመለሱ የኢትዮጵያ ዜጋ ነዎት? ከሆንክ ኢራራ በኢትዮጵያ ህይወታችሁን እንደገና እንድትጀምሩ ሊረዳህ ይችላል።
ድጋፍ ከፈለጉ ከተመለሱ በኋላ ባሉት 3 ወራት ውስጥ PAD ን ማነጋገር አለብዎት። ይህ ድጋፍ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ እስከ 12 ወራት ድረስ ይቆያል።
ድጋፍን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ነዎት? ከሆኑ ከዚህ በታች ዝርዝር አድራሻ በመጠቀም የUK IRARA ቢሮን ያነጋግሩ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ነዎት? ከሆኑ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም አዲስ አበባ የሚገኘውን የፖዘቲቭ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት (PAD) ቢሮ ያነጋግሩ።
ስለ ፕሮግራሙ፡-
በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ለመቆየት የሚያስችል ማስረጃ የሌላቸውን ሰዎች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ እና የመቀላቀል ተግባራትን ይደግፋል። ፕሮግራሙ የተለያዩ አገልግሎቶችን ያመቻቻል፣ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኅላ የረጅም ጊዜ ወይም ዘለቄታዊነት ያለው ድጋፍ ይሰጣል።
ስለ IRARA እና PAD፡
IRARA ከፖዚቲቭ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት (PAD) ጋር በመተባበየሆም ኦፊስን የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራምን በኢትዮጵያ ያስተባብራል።
PAD ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን፣ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በመላ ኢትዮጵያ ለማስፈን ይተጋል። IRARA እና PAD በጋራ በተጠቃሚው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የተዘጋጀ የባለሙያ እና የረጅም ጊዜ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ ይሰጣሉ።
በኢትዩጵያ የግኝት መረጃ / ለመነጋገር
አድራሻ፡ PAD፡
PAD ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁ. B005
ሲኤምሲ አደባባይ አካባቢ፣ ከመናብርት ሪል ስቴት 500 ፣ ፖ.ሳ.ቁ 26867/1000፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የስራ ሰአት፡ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት
ሜትር ስልክ፡
- +251-902 49 65 99
- +251-924 26 06 32
- +251-953 10 02 20 (out of hours)
IRARA በዩኬ የቢሮ ሰዓቶች:
ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8፡30 እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት
ሜትር ስልክ፡ +44 (0 )1433 627 247