Guidance

Notice of rights and entitlements Amharic (PACE Code C) (accessible version)

Updated 27 January 2020

በቁጥጥር ስር እያሉ መብቶችዎን ያስታውሱ

በዚህ መሳወቂያ ውስጥ ያሉት መብቶችጥቅሞች በእንግሊዘና በዊልስ ህግ መሰረተ የተረጋገጠ ሆኖ ከአውሮፓ የስብአዊ መብቶች ስምምነት የሚጣጣሙ EU Directive 2012/13 (ኢውሮፓ ዳይረችቲቨ 2012/13) በወንጀል ክስ ወቅት መረጃ ስለማግኘት መብት።

ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ ያሉዎት መብቶች እዚህ ገጽ ውስጥ ተጠቃልለዋል

በሚቀጥለው ገጽ ውስጥ ከፓራግራፍ1 እስከ 11 ተጨማሪ መረጃ ይገኛል።

ሙሉ ዝርዝር በፖሊስ የተግባር ስርዓተ ደንቦች ኮድ ሐ ይገኛል።

1.    ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ የጠበቃ ዕርዳታ ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይንገሩዋቸው። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።

2. የት እንዳሉ እንዲያውቁልዎት የሚፈልጉት ሰው ካለ ለፖሊሶቹ ይንገሩ። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።

3. የፖሊሶቹን የአሰራር ደንቦች መረዳት ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይንገሩ- የተግባር ስርዓተ ደንቦች ይባላሉ።

4. የህክምና እርዳታ ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይናገሩ. ከታመሙ ወይም አደጋ ከደረሰብዎ ለፖሊሶቹ ይንገሩ። የህክምና አርዳታ ነጻ ነው።

5. ስለ ተጠረጠረ ወንጀል ጥያቄ ቢጠየቁ የመናገር ግዴታ የለብዎትም። ነገር ግን ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ሊጠቅምዎት የሚችልን ነገር ሳይናገሩ በመቅረትዎ ጉዳይዎ ቀድም ባለመናገርዎ ሊጎዳ ይችላል። የሚናገሩት ሁሉ በመረጃነት ሊቀርብ ይችላል።

6. ፖሊሶች ፈጸሙ ብለው ስለሚገምቱት ወንጀል እና ለምን እነደተያዙና እንደታሰሩ ሊነግሩዎ ይገባል።

7. ፖሊሶች ለእርስዎና የሕግ ተወካይዎ ለምን እነደተያዙና እንደታሰሩ በፖሊስ ጣቢያው ስለሚቆዩበት ግዜ የሚገልጡ ሪኮርዶችና ዶኩመንቶችን ሊያሳዩዋችሁ ይገባል።

8. አስተርጓሚ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ፖሊሶች ሊያቀርቡልዎ ይገባል። አንዳንድ ዶኩመንቶችም ሊተረጎሙልዎ ይችላል። ይህም የነጻ አገልግሎት ነው።

9. ብሪታኒያዊ ካልሆኑና የአገርዎ ቆንስላ ወይም ኤምባሲ እንዲነገርልዎና እስር ላይ መሆንዎ እንዲታወቅ ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይንገሩ። ይህም የነጻ አገልግሎት ነው።

10. ፖሊሶቹ ምን ያህል ግዜ በቁጥጥር ስር ሊያውሉዎት እንደሚችሉ ሊነግሩዎት ይገባል።

11. ክስ ከቀረበብዎና ጉዳይዎ ወደ ፍርድ ቤት ከተመራ፤ እርስዎ ወይም ጠበቃዎ አቃቤ ሕግ ያለውን መረጃዎች ፍርድ ቤት ከመቅረብዎ በፊት የማየት መብት አላችሁ።

ስለነኚህ ሁሉ መብቶች ግልጽ ያልሆነልዎ ነገር ካለ ለእስረኞች ጉዳይ ኦፊሰሩ ይንገሩ።

ፖሊስ እንዴት ያለ አያያዝና እንክብካቤ ሊያደርግሎት የሚገባ የሚያስረዳ ተጨማሪ መረጃ ከማጠቃለያው ገጽ በኋላ ይመለከቱ።

ይህ ጽሑፍ እና መረጃ ስለ መብትና የሚገባችሁ ነገሮች የሚቀልጥ ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ በተግባር የሚውል ነው። ነሐሴ 21/2019

እባክዎ ይህንን መረጃ ያግኙና በአፋጣች ያንብቡት። ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ ውሳኔ ለመወሰን ይረዳዎታል።

1. የሚረዳዎትን የሕግ አማካሪ ማግኘት

  • የሕግ አማካሪዎ ሊረዳዎና የህግ ምክር አገልግሎት ሊሰጥዎ ይችላል፡፡
  • የሕግ አማካሪ ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረብዎ ስህተት የሰሩ መሆንዎን አያመለክት፡፡
  • የሕግ ድጋፍ ያስፈልግዎ እንደሆን የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ሊጠይቅዎ ይገባል፡፡የሚያገኙትም አገልግሎት ነፃ ነዉ፡፡
  • በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ቀንም ሆነ ማታ በማንኛዉም ሰዓት የሕግ ባለሙያዎች እንዲያነጋግሩ ፖሊሶች ሊፈቅዱልዎት ይገባል፡፡
  • የሕግ ምክር ድጋፍ ከጠየቁ በአብዛኛዉ ጊዜ ፖሊሶች የሕግ አማካሪዎን የማግኘት እድል እስኪያገኙ ድረስ ጥያቄ ሊጠይቁዎ አይገባም፡፡
  • የሕግ ምክር አገልግሎት እንደማያስፈልግዎ ከገለፁ በኋላ ሃሳብዎን ቢቀይሩ ለጥበቃ የፖሊስ መኮንኑ ያሳዉቁትና የሕግ አማካሪ እንዲያገኙ ይረዳዎታል፡፡
  • የሕግ አማካሪዎ ሳይመጣ ከቀረ ወይም ፖሊስ ጣቢያ ድረስ መጥቶ ካላነጋገርዎ ወይም ድጋሚ ለማነጋገር የሚፈልጉ ከሆነ ፍላጎትዎን ለፖሊስ በማሳወቅ ያግኙት፡፡

ስለአንዳንድ ቀላል ጉዳዮች ነፃ የሕግ ድጋፍ ስለሚያገኙበት ሁኔታ፡

  • አንዳንድ ቀላል ጉዳዮች ገበኑ ቀለል ያለ፡ ያለክፍያ የሕግ አማካሪ ይህ ጉዳዮች የተማረ ባለሙያ የሕግ እማካሪው ከ Criminal Defence Service (CDS) Direct (የገብን ተከራካሪ ጠበቃ ክፍል) ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሳይመጡ በስልክ ምክር ሊሰጥዎች የሚችሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ያሚያስመጣ ከታች በተዘረዘሩት ልዩ ምክንያት ሳይሆን በቀር፡
    • ፖሊሶች ስለወንጀል ጉዳይ ሊጠይቁዎት ሲፈልጉ ወይም በአይን ምስክርነትየመለየት ስራ የሚያሰሩዎት ከሆነ፤
    • ‹‹ተገቢ ከሆነ አዋቂ ሰዉ›› እርዳታ የሚሹ ከሆነ፤ ‹‹እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች›› የሚለዉን ክፍል ይመልከቱ፡፡
    • በስልክ መነጋገር ያልቻሉ ከሆነ፣ ወይም
    • በፖሊስ ከባድ የሆነ ኢ-ሥነ ምግባራዊ ድርጊት ተፈጽሞብኛል የሚሉ ከሆነ አማካሪዎ በአካል ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሊመጡ ይገባል፡፡

የነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት በቀጥታ ከ CDS (ሲ.ዲ.ኤስ) ጥብቅና አገልግሎት በስልክ ብቻ እንዲሰጥ ያልተወሰነ ከሆነ፡

  • በግልዎ የሚያዉቁትን የሕግ አማካሪ ማነጋገር የሚፈቀድልዎ ሲሆን አማካሪዎ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ስራ የሚሰሩ ከሆነ ክፍያ እንዲከፍሏቸዉ አይጠበቅብዎትም፡፡ በግልዎ የሚያዉቁት የሕግ አማካሪ ከሌለዎ ወይም መገናኘት ካልቻሉ የሕግ ድጋፍ እንዲሰጥ የተመደበዉን አማካሪ ማግኘትና ነፃ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የሕግ ድጋፍ እንዲሰጥ የተመደበዉ የሕግ አማካሪ ከፖሊስ ጋር የሚያገናኘዉ ነገር የለም፡፡

ነፃ የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማመቻቸት፡

  • ፖሊስ ወደተከላካይ Defence Solicitor Call Centre (DSCC) ጠበቆች የጥሪ ማእከል ይደዉላል፡፡ የተከላካይ ጠበቆች የጥሪ ማእከል የሚሰጥዎ የሕግ ምክር አገልግሎት በጠየቁት የሕግ አማካሪ በኩል ወይም በተረኛ ምድብ የሕግ አማካሪ በኩል መሰጠት እንዳለበት ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
  • የተከላካይ ጠበቆች The DSCC እና CDS Direct ልዩ አገልግሎት ገንዘብ የማይከፈልበት የሕግ ምክር ለመስጠት የሙያስተናግዱ ሲሆኑ ከፖሊስ ጋር ምንም ግኑኘት የላቸውም።

ለሚያገኙት የሕግ ምክር አገልግሎት ክፍያ መፈጸም ከፈለጉ፡

  • ፍላጎት ካሎት በሁሉም ጉዳዮች የሕግ ምክር ሲጠይቁ መክፈል ከመረጡ ሊከፍሉ ይችላሉ።
  • የሚያገኙት ነጻ የሕግ ምክር አገልግሎት በቀጥታ የወንጀል ጥበቃና አገልግሎት በኩል በስልክ ምክር ብቻ የተገደበ ከሆነ የሚፈልጉትን የሕግ አማካሪ በስልክ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ላገኙት የሕግ ድጋፍ የማይከፈልልዎት ከመሆኑም በላይ ራስዎ ክፍያዉን እንዲፈፅሙ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ የተከላካይ ጠበቆች የጥሪ ማእከል እርስዎን በመወከል የሕግ አማካሪዎችን ያነጋግርልዎታል፡፡
  • የግልዎ የሕግ አማካሪ በስልክ ሆነ በአካል ፖሊስ ጣቢያ ድረስ መጥተዉ ሊጠይቁ መብት አሎት፡፡
  • የመረጡትን የሕግ አማካሪ ማግኘት ካልቻሉ ፖሊስ ወደ ተከላካይ ጠበቆች የጥሪ ማእከል በመደወል ለሕግ ምክር በተመደበዉ የሕግ አማካሪ በኩል ነፃ የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ ሊያመቻችልዎት ይችላል፡፡

2. ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ መሆንዎን ለሌሎች ለማሳወቅ

  • ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ሊያሳውቁ ከፈለጉ፡ ለፖሊስ ለሚያውቁት ሰው እንዲገናኝላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። ይህ አገልግሎት ያለክፍያ ነው።
  • ፖሊሶች ግለሰቡን በአስቸኳይ እንዲያገኙ የተቻላቸዉን ያህል ጥረት ያደርግልዎታል፡፡

3. የአሰራር ደንብን ስለመመልከት

  • የ አሰራር ሕገ ደንብ ማለት በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ወቅት ፖሊሶችሊያደርጓቸዉ የሚገቡና የማይገቡትን ነገሮች የሚነግሩዎት ሕግጋት ናቸዉ፡፡
  • ፖሊስ የአሰራር ደንቡን የሚገልጥ ጽሑ Code Of Practice (ኮድ ኦፍ ፕራክቲስ) እንዲያነቡ ሲፈቅድልዎ ነገር ግን ይህንን ካላደረጉ ፖሊስ ህግን እንደጣሱ አድርጎ ሊቆጥር አይገባም፡፡
  • የአሰራር ደንቡን ለማንበብ ሲፈልጉ ለፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ያሳዉቁ፡፡

4. ከታመሙ እና ከተጎዱ የህክምና እርዳታ ስለማግኘት

  • የጤና ህክና ካሰፈለጋችሁ ወይም የሆነ የሰውነት ጉዳት ካላችሁ ለፖሊስ እንደታመሙ ያሳውቁ፡ ወይ ዶክቶር ወይም ደግሞ ነርስ ይጠርላችዋል። ይህ አገልግሎት ያለ ክፍያ ነው የሚሰጠው።
  • ምናልባት የራስዎ መድኃኒት ካሎት መውሰድ ሊፈቀድሎት ይቻላል ሆኖም ግን ፖሊስ መጀመሪያ ምርመራ ማድረጋ አለባቸው። ብዙ ግዜ፣ መጀሪያ ነርስ ታዮታለች ሆኖም ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፖሊስ ኮክተር ይጠራሎታል፡፡

5. ጥያቄ ሲጠየቁ መልስ አልመስጠት መብት

ስለተጠረጠሩበት ጥፋት በሚጠየቁ ግዜ ከተጠየቅዎት መልስ መስጠት ካልፈለጉ ዝም ማለት መብት አሎት።

ሆኖም ግን ሲጠየቁ መልስ ላልሰጡት ጉዳይዎ የሚችል ሲሆን ይህም በኋላ በፍርድ ቤት የሚጠየቁት ሊሆን ይችላል፡፡

የሚሉት ነገሮች በሙሉ እንደ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።

6. አጥፍተዋል ተብሎ ስለተጠረጠሩበት ወንጀል ማወቅ እና ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና እንደታሰሩ ማወቅ

  • ፖሊስ ፈጽመዋል ተብሎ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ምንነት ሊነግሩዎ ይገባል። ይህም መቼ እና የት ተፈጸመ ብለው እንደሚገምቱ መንገርን ይጨምራል።
  • ፖሊስ ለምን ወንጀሉን ፈጸሙ ብለው እንደገመተ እና ለምን ሊያስሩዎ እንደወሰነ መናገር አለበት፡፡
  • ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ፖሊስ ለምን በቁጥጥር ስር መዋል አለብዎ ብሎ እንዳመነ ሊነግሩዎ ይገባል።
  • ማንኛወም ዓይነት ጥየቄ ሳይቀርብልዎ በፊት ፖሊስ ራስዎን ለመከላከል እንዲችሉ፤ ለርስዎ እና ለጠበቃዎ ፈጽመዋል ብለው ስለሚያምኑት ወንጀል በቂ መረጃ መስጠት ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም የፖሊስን ምርመራ ግዜ የሚያስተጓጉል መሆን የለበትም።
  • ይህም ፖሊሶች ፈጽመዋል ብለው የሚገምቷቸውን ሌሎች ወንጀሎችም ይመለከታል።

7. እርስዎን እና በቁጥጥር ስር መዋልዎን የሚመለከቱ መዝገቦች ጽሑፍ ስለማየት

  • ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት ፖሊሶች:-
    • በቆይታ ሪኮርድዎ ውስጥ የታሰሩትን ምክንያተ እና ለምን እንዳስፈለገ እና ለምን በቁጥጥር ስር መቆየት አለብዎ ብለው እንዳመኑ መመዝገብ አለባው።
    • እርስዎ እና ጠበቃዎ እነኚህን ሪኮርዶች እንድታዩ መፍቀድ አለባቸው። የእስር ጉዳይ ኦፊሰሩ እንዲመለከቱ ይረዳል።
  • ይህም ፖሊስ ፈጽመዋል ብለው የሚገምቷቸውን ሌሎች ወንጀሎችም ይመለከታል።
  • የታሰሩበትን እና በቁጥጥር የዋሉበትን ምክንያት ሕጋዊነት በተሳካ ሁኔታ ለመከራከር እንዲያስችልዎ ፖሊሶች የሚመለከታቸውን ሰነዶችና ማቴርያሎችንእርስዎ ወይም ጠበቃዎ እነዲያዩ መፍቀድ አለባቸው

8. አስተርጓሚ እንዲጠራላችሁ ማድረግ እና የተወሰኑ ዶኩመንቶች እንዲቶረጎምላችሁ ማድረግ እንዲረዳችሁ

  • የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ወይም መረዳት የማይችሉ ከሆነ ፖሊስ የራስዎን ቋንቋ መናገር የሚችል ሰዉ እንዲረዳዎ ያመቻቻል፡፡ ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።
  • መስማት የተሳነዎ ከሆኑ ወይም የመናገር ችግር ካለብዎት የብሪታንያ የእንግሊዘኛ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ እንዲረዳዎ ያመቻችልዎታል። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።
  • እንግሊዘና የማይናገሩ ወይም የማይረዱ ከሆነ ለምን እንደታሰሩና የተከሰሱበት ወንጀል በአስተርጓሚው አማካይነት ይነግሩዎታል። ይህም ፖሊሶች ባስሩዎት ቁጥር ተግባራዊ መሆን አለበት።
  • እርስዎን ለማሰር ክወሱኑ እና በወንጀል በተከሱ ቁጥርም፡ የተለየ ምክንያት ካልኖረ በስተቀር፡ ፖሊሶች ለምን እንደታሰሩና በምን ወንጀል ክስ እንደተመሰረትብዎ የሚገልስ ወረቀት በራስዎ ቋንቋ ተተርጉሞ መሰጠት ይኖርባችዋል። ምክንያቶቹም፡
    • እርስዎ ሁኔተውን እና ሪኮርዱን አለመቀበልዎ የሚያመጣውን ችግር ተረድቻለሁ ሪኮርዱ ለራሴ መከላከያ አያስፈልገኝም ብለው ከወሰኑ፤ እነዲሁም ፖሊሶች ይህን ለመወሰን ጠበቃ እንዲያነጋግሩ ፈቅደውልዎ ከሆነ ነው። ስምምነትዎን በጽሁፍ መስጠት ይኖርብዎታል፡፡
    • ከጽሁፍ ትርጉም ይልቅ የቃል ማጠቀለያ ትርጉም ባስተርጓሚ አማካይነት መስጠት ለጉደይዎ ለመከራከርና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት በቂ ሆኖ የእስር ቤቱ ተረኛ መኮንን ከፈቀደ ነው።
  • ፖሊስ ጥያቄዎች ሲጠይቅ እና ለጠየቁት ጥያቄዎች እና መልስ በቴፕ ካልተቀዳ፡ አስተርጓሚው የዚሁ ትያቄ እና መልስ መዝገብ በቋንቋ አስተርጉሞ ሊሰጦች ይችላል። ከመፈረሞ በፊትም ትክክል መሆኑን አለመሆኑ ማረጋተጥ ይችላሉ።
  • ለፖሊስ ቃል መስጠት ከፈለጉ፡ አስተርጓሚው የቃሉ ጽሑፍ በቋንቋዎ ማስተርጎም ይችላል። ይህ ጽሑፍ አንብበዎ ትክክል መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ መፈረም ይችላሉ።
  • ይህ ማሳወቂያም እንዲተረጎምልዎ መብት አለዎት። በጽሁፍ መተርጎም ካልተቻለም መረጃው ባስተርጓሚ አማካይነት ተሰጥቶዎ ባፋጣኝ ተተርጉሞ እንዲሰጥዎ መደረግ አለበት።

9. የሐገርዎን ኤምባሲ እና ቆንስላ ስለማነጋገር

ብሪታንያዊ ካልሆኑ የት እንዳሉና ለምን ፖሊስ ጣቢያዉ ዉስጥ እንዳሉ ለማሳወቅ የአገርዎን ከፍተኛ ኮሚሽነርን፣ ኢምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንደሚፈልጉ ለፖሊስ ማሳወቅ ይችላሉ፡፡ ፖሊስ በግል ሊጎበኝዎት ወይም የሕግ አማካሪ እንዲያይዎት ሊያመቻችልዎት ይችላል፡፡

10. ለምን ያህል ጊዜ ሊታሰሩ ይችላሉ

  • በብዛት ቢያንስ ለ 24 ሰዓት ክስ ሳይቀርብሎት ሊታሰሩ ይችላሉ። ከዚሁ በላይ ሊሆን ይችላል፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ገበኑ በፍርድ ቤት ውስጥ በዳኛ እና በነዋሪዎች የሚታይ ጉዳይ ክሆን እና የ የፖሊስ ሹሙ ወይም ፍ/ቤት የሚፈቅድ ከሆነ የእስር ጊዜዉ ከዚህ በላይ ሊረዝም ያችላል፡፡ ከ36 ሰዓት በላይ ክስ ሳይመሰረትብዎ ሊቆዩ የሚችሉት ግን ፍ/ቤቱ ሲፈቅድ ብቻ ነዉ፡፡ ይህ ሂደት ማጣራት ይባላል፡፡
  • በየጊዜዉ የበላይ የፖሊስ ሹሙ በእስር መቆየት ይኖርብዎት እንደሆነ ጉዳይዎን ማጣራት አለበት፡፡ ይህ ስለጉዳይዎ ያለው አዲስ ነገር ማሳወቅ ተብሎ ይጠራል የዚህ ስራ ሐላፊ ደግሞ የጉዳይ መርማሪ ተብሎ ይጠራል። ይህ ምርመራ ተብሎ ይጠራል። በመልካም ሁኔታ ዉስጥ ካሉ ስለተወሰነብዎት የቆይታ ዉሳኔ ላይ አስተያየት የመስጠት መብት አለዎት ወይ በጽሑፍ ወይም ደግሞ በስልክ የፓሊስ ሽሙ ለምንስ እስከሐሁን ድረስ ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ መግለጫ ይሰጦታል። የሕግ አማካሪዎም እርስዎን በመወከል አስተያየቱን የመስጠት መብት አለዉ፡፡
  • ገምጋሚ ኦፊሰሩ ካልፈታዎት ለምን እንዳልተፈቱ እና የ እስር ሪኮርዱ ላይ የሰፈረውን ምክንያት መነገር አለብዎት።
  • በቁጥጥር ስር መዋልዎ አስፈላጊ ካልሆነ መፈታት አለብዎት። ፖሊስ የወንጀል ምርመራውን መቀጠል እንደፈለገ ከነገሮት በዋስ ወይም ደግሞ ያለዋስ መለቀቅ ይችላሉ። በዋስ ከወጡ እርስዎ ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው ነገር ይነገሮታል፡፡
  • ፖሊሶች በቁጥጠር ስር የሚቆዩበትን ግዜ ለማራዘም ፍርድ ቤቱን ከጠየቀ፡
    • የቴሌቭዠን ግንኙነቱ ተሰናድቶ በፍርድ ቤት ያሉ ሰዎእን እየተመለከቱና እያዳመጡ እንዲሁም ሰዎቹምነተ እርሶን እየተመለከቱና እያዳመጡ ካልሆነ በስተቀር ወደ ፍርድ ቤት መምጣት ይኖርቦታል፡፡
    • የተለቪዥን ግንኙነቱ ሊካሄድ የሚችለው በዚህ መንገድ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብዎ አስፈላጊ ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ ብቻ ሲሆነ ይህም የሚወሰነው በየፖሊስ ጣቢያ ሹም ነው።
    • ፖሊሶች ለምን እርስዎን በቁጥጥር ስር መቆየት እንዳለብዎ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ምክንያት እና መረጃ ግልባጭ ለእርስዎ መሰጠት አለበት።
    • ፍርድ ቤት ችሎት ሲቀርቡም ጉድያዎ እንዲታይሎት ጠበቃ አብሮዎ እንዲሆን መብት አለዎት።
    • ፖሊሶች በቁጥጥር ስር እንዲየቆዩዎ የሚፈቀደው ፍርድ ቤቱ አስፈላጊነቱን ሲ ያምን እና ፖሊሶች ጉዳዩን በጥንቃቄ እየመረመሩ እንደሆነ እና ግዜ እንደማያጠፉ ካመነ ብቻ ነው።
  • ፖሊሶች ፍርድ ቤት ለማቅረብ በቂ መረጃ ካላቸው ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ እያሉ ወይም በደብዳቤ ክስ ይመሰረትብዎ እና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡና እንዲፈረድብዎ ይሆናል።

11. ጉዳዮ ፍርድ ቤት ሲቀርብ መረጃ የማየት ፍቃድ

ባጥፊነት ክስ ከተመሰረተብዎት እርስዎ እና ጠበቃዎ የቀረበብዎን መረጃ እና ለመከራከሪያ የሚረዳዎትን መረጃ እንድታዩ ሊፈቀድላችሁ ይገባል። ይህም ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከመታየቱ በፊት መደረግ ፖሊሶችና አቃቤሕግ እነኚህን መረጃዎች እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እንዲያዩና እንዲያገኙ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።

ፖሊስ ጣቢያ እያላችሁ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ማወቅ የሚገባችሁ ነገሮች።

ሊደረግልዎ ስለሚገባ አያያዝና እንክብካቤ

እነዚህ ፅሁፎች በፖሊስ ጣቢያ በሚቆዩበት ወቅት ምን ሊጠብቁ እንደሚገባ የሚነግሮዎት ናቸዉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የፖሊስ አሰራር ደንቡን ይመልከቱ፡፡ ፅሁፎቹ ከታች ስለተገለፁ ነገሮች ተጨማሪ መረጃ የት እንደሚያገኙ የሚገልፁ ናቸዉ፡፡ ጥያቄ ካለዎ የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑን ያነጋግሩት፡፡

እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች

  • እድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ተጋላጭ የሆነ ሲሆን፣ ትምህርት የመቀበል ችግር ካለብዎ እና በቀላሉ በአደጋ ሊወድቁ የሚችሉ ከሆነወይም የአእምሮ ጤና ችግር ካለብዎ ፖሊሶች ስራቸዉን ሲሰሩ ከጎንዎ መብት አሎት ሰዉ ያስፈልግዎታል፡፡ ይህም ሰዉ ‹‹ተገቢነት ያለዉ አዋቂ ሰዉ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ የዚሁ ግልባጭ መግለጫ ይሰጦታል።
  • ፖሊሶች ስለመብትዎና ለምን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሲነግርዎ የርስዎ ተገቢ አዋቂ ሰዉ አብርዎት ሊሆን ይገባል እናም ምን ምን እየተካሄደ እንዳለ እና ስለእርስዎ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች በደንብ እንዲረዳዎት ይረዳዎታል፡፡ የፖሊስ ጥንቃቄ በሚነበብልዎት ጊዜም ይህ ሰዉ አብሮዎት መሆን ይገባዋል፡፡
  • ተገቢው አዋቂ ሰው ርስዎን በመወከል የሕግ አማካሪዎን ሊያነጋግረልዎ ይችላል፡፡
  • የሚፈልጉም ከሆነ ተገቢዉ አዋቂ ሰዉ ክፍልዎ ዉስጥ በሌለበት የሕግ አማካሪዎን ማነጋገር ይችላሉ፡፡
  • ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ባሉበት ወቅት ፖሊስ ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ለማድረግ ይፈልግ ይሆናል፡፡ የተለየ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ፖሊስ የሚከተሉትን ነገሮች በሚያደርጉበተ ወቅት የእርሶ ተገቢነት ያለዉ አዋቂ ሰዉ አብርዎት ሊኖር ይገባል፡፡
    • ቃለመጠይቅ ሲያደጉዎት ወይም የፅሁፍ መግለጫ ወይም የፖሊስ ማስታወሻ እንዲፈረሙ ሲጠይቅዎት፡፡
    • ከላይ ከለበሱት ውጪ ለፍተኛ ልብሶን እንዲያወልቁ ከጠየቁዎት፡፡
    • አሻራዎ ፎቶግራፍዎ ወይም ዲ ኤን ኤ ወይም ሌላ ናሙና ይወሰዳል።
    • ኤላ ተጨማሪ አስፈላጊ የሆነ ምርመራ ስለ ተጨማሪ የአይነምስክር መለያ አገባብ አሰራር መንገድ።
  • ፖሊስ ለተጨማሪ ግዜ መታሰር እንዳለቦት ለማወቅ ጉዳዮትን በሚተመግም ግዜ የእርሶ ተገቢ አዋቂ ሰው በአካል ወይም በስልክ በመገኘት ለማገዝ እድል መስጠት አለበት፡፡
  • ተገቢ አዋቂ ተወካይዎ የሚገኙ ከሆነ ፖሊሶች በጥፋተኝነት ክስ በሚያቀርቡብዎ ግዜ ዕድል ሊሰጣቸው ይገባል።

በፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ስለመቆየት ሊያዉቋቸዉ የሚገቡ ሌሎች ነገሮች የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ ጊዜዎን ዝርዝር ማግኘት

  • በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ላይ የሚሆን ማንኛዉም ነገር ይመዘገባል፡፡ ይህ የጥበቃ መዝገብ ይባላል፡፡
  • ከፖሊስ ጣቢያዉ ሲወጡ ርስዎ፣ የርስዎ የሕግ አማካሪ ወይም ተገቢ የሆነ አዋቂ ሰዉ የጥበቃ መዝገቡን ግልባጭ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ፖሊሶች የጥበቃ መዝገቡን በተቻለ ፍጥነት ሊሰጥዎ ይገባል፡፡
  • የጥበቃ መዝገቡን ግልባጭ ከፖሊስ ጣቢያዉ ከወጡ እስከ 12 ወራት ድረስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ለቀጣይ ግኑኘት

  • አብዛኛዉን ጊዜ የሕግ አማካሪ ለማነጋገርም ይሁን መታሰርዎን ለሌላ ሰዎች ለማሳወቅ ሲፈልጉ አንድ የስልክ ጥሪ እንዲያደርጉ ይፈቀድልዎታል፡፡
  • ስልክ የሚፈልጉ ከሆነ ለፖሊስ ያሳዉቁ፡፡
  • እስክሪብቶና ወረቀትም ከፈለጉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ሰዎች በእስር እንዳሉ ሊጎበኙዎት የሚችሉ ቢሆንም ይህንን ግን የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ሊከለክል ይችላል፡፡

የእስር ክፍል

  • የሚቻል ከሆነ በራስዎ ክፍል ብቻ መሆን ይኖርቦታል፡፡
  • ንጹህ፣ ሞቃትና ብርሀናማ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • መኝታዎ ንጹህና የተሰናዳ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • መፀዳጃ ቤትና የመታጠቢያ አገልግሎትም ሊያገኙ ይገባል፡፡

የግል ፍላገቶች - ጤና፣ ንጽሕና እና ደኅንነት

  • በቁጥትረ ስር በሚውሉበት ጊዜ እርስዎን የሚመለከቱ ወይም ስለ ጤናዎ፣ ንፅህናዎ እና ደህንነትዎ ስለሚመለከቱ ማናቸውም የግል ፍላጎቶች ከእስር ጥበቃ ባለሙያው አባል ጋር በግል ለመነጋገር ከፈለጉ መጥየቅ ይኖርብዎታል።
  • ፖሊስ ለእርሶ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ያቀርብሎታል፡፡የሚያናግሮት ሰው ከእርሶ ጋር ተመሳሳይ ጾታ ያለው እንዲሆን ከፈለጉ ያን መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • እድሜዎ 18 አመትና ከዛ በላይ የሆኑ እንስት ከሆኑ በቁጥጥር ስር እያሉ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች እንደሚፈልጉ ወይም ሊያስፈልጎት እንደሚችል መናገር ይኖርቦታል፡
    • ምርቶቹ ያለክፍያ ይሰጣሉ፣
    • ተተኪ ምርቶች ይኖራሉ፣ እና
    • የእስር ቤት የጥበቃ መኮንኑ ከተስማማ ምርቶቹን በቤተስብዎ ወይም በጓደኞችዎ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
  • በእስር ቤት ውስጥ ካሉና ከ 18 ዓመት በታች የሆንሽ ልጃገረድ ከሆንሽ የፖሊስ መኮንኑ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ያለች አንድ ሴት አንቺን ለመንከባከብና ስለ ግል ፍላጎትሽና የወር አባባ ምርቶች መጠየቅሽን ታረጋግጣለች፡፡

አልባሳት

የግል አልባሳትዎ ከተወሰደብዎት ምትክ አልባሳት ፖሊስ ሊሰጥዎ ይገባል፡፡

ምግብና መጠጥ

በቀን ሶስት ጊዜ ምግብ ከመጠጥ ጋር ሊቀርብልዎ ይገባል፡፡ ከምግብ ሰአት ዉጭም የሚጠጣ ነገር ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰዉነት እንቅስቃሴ

የሚቻል ከሆነ በየቀኑ ደጅ ወጥተው እንዲናፈሱና ንጹህ አየር እንዲያገኙ ሊፈቀድልዎ ይገባል፡፡

በፖሊስ ምርመራ ወቅት፡-

  • ክፍሉ ንፁህ፣ በቂ ሙቀትና ብርሃን ያለበት ሊሆን ይገባል፡፡
  • ሊቆሙ አይገባም፡፡
  • መርማሪ ፖሊሶቹ ስማቸዉንና ማዕረጋቸዉን ሊነግርዎት ይገባል፡፡
  • በተለመደዉ የመመገቢያ ሰአት እና በየሁለት ሰአቱ የሚጠጣ ነገር ለመዉሰድ የእረፍት ጊዜ ሊሰጥዎት ይገባል፡፡
  • በፖሊስ ጥበቃ ዉስጥ ሲቆዩ በ24 ሰዓት ዉስጥ በትንሹ 8 ሰዓት እንዲያርፉ ሊፈቀድልዎ ይገባል፡፡

የእምነት ጉዳዮች

ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ እምነትዎን ለማምለክ የሚያስፈልጉዎ ነገሮች ካሉ ለፖሊሶች ይናገሩ። የሃይማኖት መጽሐፍትና ሌሎችም እቃዎችን በማቅረብሊረዱዎ ይችላሉ።

የተለመዱ ሕጎች የሚቀየሩበት ጊዜያት

የሚረዳዎ የሕግ አማካሪ ማግኘት

የሕግ አማካሪዎን ከማግኘትዎ በፊት ፖሊስ በአስቸኳይ ጥያቄ ሊጠይቅዎ የሚፈልግበት አንዳንድ ልዩ አጋጣሚዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለነዚህ ልዩ ሁኔታዎች መረጃ በአሰራር ደንቡ ዉስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡ ይህ መጽሐፍ በፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ፖሊስ ምን ማድረግና አለማድረግ እንዳለበት የሚያስቀምጥ ነዉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡ ክፍል ሲ አንቀፅ 6.6 ዉስጥ ተካቶ ይገኛል።

ፖሊስ የመረጡትን የሕግ አማካሪዎትን እንዳያነጋግሩ ሊከለክልዎት የሚችልበት አንድ ልዩ ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ሌላ አማካሪ እንዲመርጡ ሊፈቅድልዎ ይገባል፡፡ ዝርዝሩን መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡን ክፍል ቢ አባሪ ቢ ላይ አሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ለሌሎች ስለማሳወቅ

ፖሊስ ከማንም ሰዉ ጋር እንዳይገናኙ ሊከለክልዎ የሚችልበት ልዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ልዩ ሁኔታዎች በአሰራር ደንቡ ዉስጥ ተካተዉ ይገኛሉ፡፡ ዝርዝሩን መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡን ምዕራፍ ሲ አባሪ ቢን ይመልከቱ፡፡

ጠጥቶ ማሽከርከርና እጽ ወስዶ የማሽከርከር ጥፋት

ጠጥቶ በማሽከርከር ወይም እጽ ወስዶ በማሽከርከር ወንጀል ተጠርጥረዉ የታሰሩ ከሆነ የሕግ አማካሪዎን የማነጋገር መብት አለዎት፡፡ ነገር ግን የሕግ ባለሙያዎን ቀድመዉ ባያነጋግሩም ፖሊስ ሲጠይቅዎ የትንፋሽ፣ ደም ወይም ሽንት ናሙና ለመስጠት እምቢ የማለት መብት የለብዎትም፡፡

በ1983 የአእምሮ ጤና ሕግ መሰረት የሚፈጸም እስር

ፖሊስ ለአእምሮ ጤና ሕግ ግምገማ ብሎ ማሰር የሚችል ሲሆን እድሜዎ ከ 18 አመትና ከዛ በላይ ሆኖ ባህሪዮትም በእርሶ ወይም በሌላ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞት ለማስከተል ምክንያት የሚሆን ከሆነ በሌላ ቦታ ምክንያታዊ መሆን ካልቻሉ ነው፡፡ በአእምሮ ጤና ሕግ መሰረት ከታሰሩ በጥፋት ታስረዋል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡

ይህም ማለት ፖሊስ በዶክተር እና የሙያ ብቃቱ በተረጋገጠ የአእምሮ ጤና ባለሞያ እንዲመረመሩ ሊያመቻችልዎ ይገባል ማለት ነዉ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ከደረሱ ወይም ከታሰሩ በ24 ሰዓት ዉስጥ ምርመራዉ ሊካሄድልዎ የሚገባ ሲሆን ፖሊስ ምርመራዉ በተቻለ ፍጥነት የሚካሄድበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ይህ የ 24 ሰዓቶች በፖሊስ ጣቢያ የሚቆይበት ሁኔታ ተጨማሪ 12 ሰዓቶች ሊጨምርቦት ይችላሉ ምናልባት ዶክተር አስፈላጊ የሆነ ምርመራዎች እኒፈጽሙ እንዲያስችላቸው እና ይህ ከሆነ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለው ፖሊስ ይህ እንዲሆን ፍቃድ መስጠት አለበት። በዚህ ጊዜ ምርመራዉን ለማካሄድ ይመች ዘንድ ወደ ተሻለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ፖሊስ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ምርመራዉ ከመካሄዱ በፊት ፖሊስ ብቃታቸዉ የተረጋገጠ የጤና ጥበቃ ሰራተኞች እንዲያዩዎ ሊያመቻች ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ምርመራ ማካሄድ ባይችሉም በጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያና ምርመራዉ ምን ማለት እንደሆነ በማብራራት ሊያግዙዎ ይችላሉ፡፡

ነፃ እስረኛ ጎብኝዎች

በድንገት ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ በመዝለቅ እስረኞችን እንዲጎበኙ የተፈቀደላቸዉ ነፃ የእስረኛ ጎብኝዎች የተባሉ በጎ ፈቃደኛ የማህበረሰብ አባላት አሉ፡፡ ስራቸዉም እስረኞች በአግባቡ መያዛቸዉንና መብቶቻቸዉ የተጠበቁላቸዉ መሆኑን ማረጋገጥ ነዉ፡፡

ነፃ እስረኛ ጎብኝዎች ጋር ልገናኝ ወይም መጥተዉ ይጎብኙኝ ብለዉ የመጠየቅ መብት የለዎትም፡፡ ነገር ግን በፖሊስ ጥበቃ ስር እያሉ ጎብኝዎቹ እርስዎን የመጎብኘት አጋጣሚ ካገኙ ከፖሊስ ተፅዕኖ ነፃ በሆነ ሁኔታ የእርስዎ ደህንነትና መብትዎ መጠበቁን ያረጋግጣሉ፡፡ ማጋገር ካልፈለጉ አላነጋግራቸዉም ሊሉ ይችላሉ፡፡

ስለ ቅሬታ አቀራረብ

ስለተደረገልዎ አያያዝ ቅሬታ ለማቅረብ ከፈለጉ መርማሪ ፖሊሱን ወይም ከፍ ያለ ማዕረግ ያለዉን ፖሊስ ለማነጋገር ይጠይቁ፡፡ ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ቅሬታዎን ማቅረብ ቢፈልጉ ኢንድፐንደንት ኦፊስ ፎር ፖሊስ (Independent Office for Police) ለነፃ የፖሊስ ቅሬታ ሰሚ ኮሚሽን ወይም በሕግ አማካሪዎ በኩል ወይም የፖርላማ አባልዎ አማካኝነት መጠየቅ ይችላሉ።