Guidance

Notice of rights and entitlements Amharic (PACE Code H) (accessible version)

Updated 11 March 2019

በዚህ መሳወቂያ ውስጥ ያሉት መብቶች በእንግሊዘና በዌልስ ህግ መሰረት የተረጋገጠ ሆኖ ከአውሮፓ የስብአዊ መብቶች ስምምነት ጋር የሚጣጣሙ የEU Directive 2012/13 (ኢውሮፓ ዳይረችቲቨ 2012/13) በወንጀል ክስ አካሄዶች ጊዜ መረጃ የማግኘት መብትን ይመለከታል።

ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ ያሉዎት መብቶች እዚህ ገጽ ውስጥ ተጠቃለዋል፡፡

በሚቀጥሉት ገፆች ውስጥ ከአንቀፅ1 እስከ 11 ተጨማሪ መረጃ ይገኛል።

ሙሉው ዝርዝር በፖሊስ የተግባር ስርዓተ ደንቦች ኮድ ሸ (H) ላይ ይገኛል።

  1. ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ የጠበቃ ዕርዳታ ከፈለጉ ለፖሊስ ይንገሩ። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።

  2. የት እንዳሉ እንዲያውቁልዎት የሚፈልጉት ሰው ካለ ለፖሊስ ይንገሩ። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።

  3. የፖሊስን የአሰራር ደንቦች መረዳት ከፈለጉ ለፖሊስ ይንገሩ- የተግባር ስርዓተ ደንቦች ይባላሉ።

  4. የህክምና እርዳታ ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይናገሩ። ከታመሙ ወይም አደጋ ከደረሰብዎ ለፖሊሶቹ ይንገሩ።የህክምና አርዳታ ነጻ ነው።

  5. ስለተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀም፣ መካፈል ወይም ለነኝህ ድርጊቶችመሳካት እርዳታ ስለመስጠት፣ መዘጋጀት ወይም ሽብር እንዲፈጠር ሌሎችን ስለማበረታታት፣ ጥያቄቢጠየቁ፣ ምንም ነገር መናገረር የለብዎትም።ነገርግን ፍርድቤት ሲቀርቡ ሊጠቅምዎት የሚችልን ነገር ሳይናገሩ በመቅረትዎ ጉዳይዎ ቀድመው ባለመናገርዎ ሊጎዳ ይችላል። የሚናገሩት ሁሉ በመረጃነት ሊቀርብ ይችላል።

  6. ተሳትፈውበታል ተብሎ ስለተጠረጠረው የሽብርተኝነት ድርጊቶች፣ በኮምሽን፣ የማዘጋጀት ወይም የማነሳሳት ተግባራት እንዲሁም ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና እንደታሰሩ ፓሊስ ለእርስዎ ሊነግርዎ ይገባል።

  7. ፖሊሶች ለእርስዎ እና ለሕግ ተወካይዎ ለምን እንደተያዙና እንደታሰሩ በፖሊስ ጣቢያው ስለሚቆዩበት ጊዜ የሚገልጡ ሪኮርዶችና ሰነዶችን ሊያሳዩዋችሁ ይገባል።

  8. አስተርጓሚ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ፖሊስ ሊያቀርብልዎ ይገባል። አንዳንድ ሰነዶችም ሊተረጎሙልዎ ይችላል። ይህም የነጻ አገልግሎት ነው፡፡

  9. ብሪታኒያዊ ካልሆኑና ለአገርዎ ቆንስላ ወይም ኤምባሲ እንዲነገርልዎና እስር ላይ መሆንዎ እንዲታወቅ ከፈለጉ ለፖሊሶቹ ይንገሩ። ይህም የነጻ አገልግሎት ነው።

  10. ፖሊስ ምን ያህል ግዜ በቁጥጥር ስር ሊያውልዎት እንደሚችል ሊነግሩዎት ይገባል።

  11. ክስ ከቀረበብዎና ጉዳይዎ ወደ ፍርድቤት ከተመራ፤እርስዎ ወይም ጠበቃዎ አቃቤሕግ ያለውን መረጃዎች ፍርድቤት ከመቅረብዎ በፊት የማየትመብት አላችሁ።

ስለነኚህ ሁሉመብቶች ግልፅ ያልሆነልዎ ነገር ካለ ለጥበቃ ፓሊስ መኮንኑ ይንገሩ።

ፖሊስ እንዴት ያለ አያያዝና እንክብካቤ ሊያደርግሎትእንደሚገባ የሚያስረዳ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የማጠቃለያውን የኋላ ገጽ ይመለከቱ።

ይህ የመብቶች እና የጥቅማጥሞች ማሳወቂያ ቅጂ ታህሳስ 1 ቀን 2018 ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል።

እባክዎ ይህንን መረጃ ያግኙና በአፋጣኝ ያንብቡት። ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ ውሳኔዎችን ለመውሰድ ይረዳዎታል።

1. የሚረዳዎትን የሕግ አማካሪ ማግኘት

  • የሕግ አማካሪዎ እገዛ ሊያደርግልዎ እና የህግ ምክር አገልግሎት ሊሰጥዎ ይችላል።
  • የሕግ አማካሪ ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረብዎ ስህተት የሰሩ መሆንዎን አያመለክትም።
  • የሕግ ድጋፍ ያስፈልግዎ እንደሆን የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ሊጠይቅዎ ይገባል፡፡የሚያገኙትም አገልግሎት ነፃ ነዉ።
  • በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ቀንም ሆነ ማታ በማንኛውም ሰዓት የሕግ ባለሙያዎችእንዲያነጋግሩ ፖሊሶች ሊፈቅዱልዎት ይገባል።
  • የሕግ ምክር ድጋፍ ጠይቀዉ ከሆነ በአብዛኛዉ ጊዜ ፖሊሶች የሕግ አማካሪዎን የማግኘት እድል እስኪያገኙ ድረስ ጥያቄ ሊጠይቁዎ አይገባም።ፓሊስ ጥያቄዎች በሚጠይቅዎ ጊዜ የህግ አማካሪ በክፍል ውስጥ እንዲኖር መጠየቅ ይችላሉ።
  • ለፓሊስ የሕግ ምክር አገልግሎት እንደማያስፈልግዎ ከገለፁ በኋላ ሃሳብዎን ቢቀይሩ፣ ለጥበቃ የፖሊስ መኮንኑ ያሳውቁትና የሕግ አማካሪ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።
  • የሕግ አማካሪዎ ሳይመጣ ከቀረ ወይም ፖሊስ ጣቢያ ድረስ መጥቶ ካላነጋገርዎ ወይም ድጋሚ ለማነጋገር የሚፈልጉ ከሆነ ፍላጎትዎን ለፖሊስ በማሳወቅ ያግኙት።
  • እርስዎ የሚያውቁት የሕግ አማካሪ ጋር መነጋገር ከመረጡ ምንም የሚከፍሉት ክፍያ የለም ጠበቃው ከህጋዊ ድጋፍ (ሌጋል ኤይድ) እርዳታ በመንግስት የሚከፈል የሚሰሩ ከሆነ። እርስዎ የሚያውቁት የሕግ አማካሪ ከሌለ በቀኑ በስራ ውስጥ የሚገኝ የሕግ አማካሪ ይጠራሎታል። ይህ አገልግሎት ነጻ ነው።
  • በስራ ላይ የሚገኝ የሕግ አማካሪ ከፖሊስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

ነፃ የሕግ ምክር እንዲያገኙ ለማመቻቸት፦

  • ፖሊስ ወደተከላካይ የህግ አማካሪ የጥሪ ማእከል(Defence Solicitor Call Centre (DSCC))ይደውላል። በDSCC የሚሰጥዎ የሕግ ምክር አገልግሎት በጠየቁት የሕግ አማካሪ በኩል ወይም በተረኛ ምድብ የሕግ አማካሪ በኩል መሰጠት እንዳለበት ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
  • DSCC ገለልተኛ የህግ ምክር አገልግሎት ሰጭ ሲሆን ገንዘብ የማይከፈልበት የሕግ ምክር የሚሰጡ ሲሆን ከፖሊስ ጋር ምንም ግኑኘት የላቸውም።

ለሚያገኙት የሕግ ምክር አገልግሎት ክፍያ መፈጸም ከፈለጉ፦

  • በሁሉም ጉዳዮች የሕግ ምክር ሲጠይቁ መክፈል ከመረጡ ሊከፍሉ ይችላሉ።
  • DSCC እርስዎን በመወከል የቀረበውን የህግ አማካሪ ያነጋግራል።
  • ከመረጡት የህግ አማካሪ ጋር በስልክ ወይም በአካል ወደ ፖሊስ ጣቢያው በመምጣት በግል የማናገር መብት አሎት፡፡
  • የመረጡትን የሕግ አማካሪ ማግኘት ካልቻሉ ፖሊስ ወደ DSCC በመደወል ለሕግ ምክር በተመደበዉ የሕግ አማካሪ በኩል ነፃ የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ ሊያመቻችልዎት ይችላል፡፡

2. ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ መሆንዎን ለሌሎች ለማሳወቅ

  • ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ለሆነ ሰው ሊያሳውቁ የሚፈልጉ ከሆነ ፖሊስ ለሚያውቁት ሰው እንዲነገርልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ይህ አገልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው።
  • በሚችሉት ፍጥነት ግለሰቡን በማግኘት ይነግራሉ።

3. የአሰራር ደንብን ስለመመልከት

  • የአሰራር ሕገ ደንብ ማለት በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ወቅት ፖሊሶችሊያደርጓቸዉ የሚገቡና የማይገቡትን ነገሮች የሚነግሩዎት ሕግጋት ናቸዉ። በዚህ ማሳወቂያ ውስጥ የተጠቃለሉትን መብቶች ዝርዝር ያካተቱ ናቸው።
  • ፖሊስ የአሰራር ደንቡን እንዲያነቡ ሲፈቅድልዎ ሕግ መጣስዎን ለማወቅ እስኪያቅታቸዉ ድረስ እያነበቡ ሊቆዩ አይገባም።
  • የአሰራር ደንቡን ለማንበብ ሲፈልጉ ለፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ያሳዉቁ።

4. ከታመሙ እና ከተጎዱ የህክምና እርዳታ ስለማግኘት

  • ህመም የሚሰማዎ ከሆነ ወይም መድሃኒት የሚፈልጉ ከሆነ አልያም ጉዳት ከደረሰብዎ ለፓሊስ ይንገሩ። ወይ ዶክተር ወይም ደግሞ ነርስ ወይም የጤና አጠባበቅ ባለሞያ ይጠራሉ እንዲሁም ይህ አገልግሎትከክፍያ ነፃ ነው የሚሰጠው።
  • የራስዎን መድኃኒት ካሎት መውሰድ ሊፈቀድልዎት ይቻላል ሆኖም ግን ፖሊስ መጀመሪያ ምርመራ ማድረግ አለበት። አብዛኛውን ጊዜ በመጀመሪያ ነርስ ያይዎታል፣ ሆኖም ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፖሊስ ዶክተር ይልካል። ሌላ ዶክተር እንዲያይዎት መጠየቅ ይችላሉ ነገር ግን ለዚህ መክፈል ያስፈልግዎት ይሆናል።

5. ጥያቄ ሲጠየቁ መልስ ያለመስጠት መብት

ተሳትፈውበታል ተብሎ ስለተጠረጠረው የሽብርተኝነት ድርጊቶች፣ ኮምሽን የመስጠት፣ የማዘጋጀት ወይም የማነሳሳት ተግባራት ጥያቄዎች ከተጠየቁ፣ ምንም ነገር ማለት አይገባዎትም።

ሆኖም ግን ሲጠየቁ መልስ ላልሰጡት ጉዳይዎ ለመከራከር ሲፈልጉ ሊጎዳዎት የሚችል ሲሆን ይህም በኋላ በፍርድ ቤት የሚጠየቁት ሊሆን ይችላል፡፡

ማንኛውም የሚናገሩት ነገር እንደ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።

6. ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና እንደታሰሩ ማወቅ

  • ፖሊሶች ፈጽመዋል ተብሎ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ምንነትሊነግሩዎ ይገባል። ተሳትፈውበታል ተብሎ ስለተጠረጠረው የሽብርተኝነት ድርጊቶች፣ ኮምሽን የመስጠት፣ የማዘጋጀት ወይም የማነሳሳት ተግባራት ፖሊሶቸችለምንወንጀሉንፈጸሙብለውእንደሚገምቱእናለምንሊያስሩዎእንደወሰኑመንገርአለባቸው።
  • ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ፣ ፖሊሶቹ ለምን በቁጥጥር ስር መዋል አለብዎ ብሎ እንዳመነ ሊነግሩዎ ይገባል።
  • ማንኛወም ዓይነት ጥየቄ ሳይቀርብልዎ በፊት ፖሊስ ራስዎን ለመከላከል እንዲችሉ፤ ለእርስዎ እና ለጠበቃዎ ፈጽመዋል ብለው ስለሚያምኑት የሽብር ድርጊት በቂ መረጃ መስጠት ይኖርበታል፤ሆኖም የፖሊስን ምርመራ ግዜ የሚያስተጓጉል መሆን የለበትም።
  • ይህም ፖሊሶች ፈጽመዋል ብለው የሚገምቷቸውን ሌሎች ወንጀሎችም በሙሉ ይመለከታል።

7. እርስዎን እና በቁጥጥር ስር መዋልዎን የሚመለከቱ መዝገቦች እና ሰነድ ስለመመልከት

  • ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት ፖሊሶች፦
    • በቆይታ ሪኮርድዎ ውስጥ የታሰሩበትን ምክንያት እና ለምን እንዳስፈለገ እንዲሁም ለምን በቁጥጥርስር መቆየት አለብዎ ብለው እንዳመኑ መመዝገብ አለባው።
    • እርስዎ እና ጠበቃዎ እነኚህን ሪኮርዶች እንድታዩ መፍቀድ አለባቸው። የጥበቃ ፓሊስ መኮንኑ ይህንን ያስተካክላል።
  • የታሰሩበትን እና በቁጥጥር የዋሉበትን ምክንያት ሕጋዊነት በተሳካ ሁኔታ ለመከራከር እንዲያስችልዎ ፖሊሶች የሚመለከታቸውን ዶኩመንቶች እና ማቴርያሎችን እርስዎ ወይም ጠበቃዎ እነዲያዩ መፍቀድ አለባቸው

8. አስተርጓሚ እንዲጠራላችሁ ማድረግእና የተወሰኑ ዶኩመንቶች እንዲቶረጎ ምላችሁ ማድረግ እንዲረዳችሁ

  • የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ወይም መረዳት የማይችሉ ከሆነ ፖሊስ የራስዎን ቋንቋ መናገር የሚችል ሰዉ እንዲረዳዎ ያመቻቻል፡፡ ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።
  • መስማት የተሳነዎ ከሆኑ ወይም የመናገር ችግር ካለብዎት የብሪታንያ የእንግሊዘኛ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ እንዲረዳዎ ያመቻችልዎታል። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።
  • እንግሊዘና የማይናገሩ ወይም የማይረዱ ከሆነ ለምን እንደታሰሩና የተከሰሱበት ወንጀል በአስተርጓሚው አማካይነት ይነግሩዎታል። ይህም ፖሊሶች ባስሩዎት ቁጥር ተግባራዊ መሆን አለበት።
  • እርስዎን ለማሰር ክወሱኑ እና በወንጀል በተከሱ ቁጥርም፡ የተለየ ምክንያት ካልኖረ በስተቀር፡ ፖሊሶች ለምን እንደታሰሩና በምን ወንጀል ክስ እንደተመሰረትብዎ የሚገልስ ወረቀት በራስዎ ቋንቋ ተተርጉሞ መሰጠት ይኖርባችዋል። ምክንያቶቹም፡
    • እርስዎ ሁኔተውን እና ሪኮርዱን አለመቀበልዎ የሚያመጣውን ችግር ተረድቻለሁ ሪኮርዱ ለራሴ መከላከያ አያስፈልገኝም ብለው ከወሰኑ፤ እነዲሁም ፖሊሶች ይህን ለመወሰን ጠበቃ እንዲያነጋግሩ ፈቅደውልዎ ከሆነ ነው። ስምምነትዎን በጽሁፍ መስጠት ይኖርብዎታል፡፡
    • ከጽሁፍ ትርጉም ይልቅ የቃል ማጠቀለያ ትርጉም ባስተርጓሚ አማካይነት መስጠት ለጉደይዎ ለመከራከርና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት በቂ ሆኖ የእስር ቤቱ ተረኛ መኮንን ከፈቀደ ነው።
  • ፖሊስ ጥያቄዎች ሲጠይቅ እና ለጠየቁት ጥያቄዎች እና መልስ በቴፕ ካልተቀዳ፡ አስተርጓሚው የዚሁ ጥያቄ እና መልስ መዝገብ በቋንቋ አስተርጉሞ ሊሰጦች ይችላል። ከመፈረሞ ከመፈረምዎ ትክክል መሆኑን አለመሆኑ ማረጋተጥ ይችላሉ።
  • ለፖሊስ ቃል መስጠት ከፈለጉ፣ አስተርጓሚው የቃሉ ጽሑፍ በቋንቋዎ ማስተርጎም ይችላል። ይህ ጽሑፍ አንብበዎ ትክክል መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ መፈረም ይችላሉ።
  • ይህ ማሳወቂያም እንዲተረጎምልዎ መብት አለዎት። በጽሁፍ መተርጎም ካልተቻለም መረጃው ባስተርጓሚ አማካይነት ተሰጥቶዎ ባፋጣኝ ተተርጉሞ እንዲሰጥዎ መደረግ አለበት።

9. የሐገርዎን ኤምባሲ እና ቆንስላ ስለማነጋገር

ብሪታንያዊ ካልሆኑ የት እንዳሉና ለምን ፖሊስ ጣቢያዉ ዉስጥ እንዳሉ ለማሳወቅ የአገርዎን ከፍተኛ ኮሚሽነርን፣ ኢምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንደሚፈልጉ ለፖሊስ ማሳወቅ ይችላሉ፡፡ ፖሊስ በግል ሊጎበኝዎት ወይም የሕግ አማካሪ እንዲያይዎት ሊያመቻችልዎት ይችላል፡፡

10. ለምን ያህል ጊዜ ሊታሰሩ ይችላሉ

  • ፍርድ ቤት ለፖሊስ ከፈቀደ ብቻ ክስ ሳይመሰረትቦት ከ 48 ሰአታት በላይ ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ያለምንም ክስ እስሩ ቢበዛ እስከ 14 ቀናት ድረስ እንዲጸና ሊያደርግ ይችላል፡፡
  • በየጊዜዉ የበላይ የፖሊስ ሹሙ በእስር መቆየት ግድ እንደሆነ ጉዳይዎን ያጣራል፡፡ ይህ ደግሞ በፖሊስ ጣቢያ ነው። ይህም ምርመራ ተብሎ ይጠራል። ስለዚህ ሁኔታ የሚመረምር ጸሐፊ ደግሞ የግምገማ መኮንን (Review Officer) ምርመር ይሚያደርግ ጸሓፊ፡ በመልካም ሁኔታ ዉስጥ ካሉ ስለተወሰነብዎት የቆይታ ዉሳኔ ላይ አስተያየት የመስጠት መብት አለዎት፡፡ የሕግ አማካሪዎም እርስዎን በመወከል ስለዉሳኔዉ አስተያየቱን የመስጠት መብት አለዉ፡፡
  • የግምተማ መኮንኑ ካልፈታዎት ለምን እንዳልተፈቱ እና የእስር ሪኮርዱ ላይ የሰፈረውን ምክንያት ሊነገርዎት ይገባል፡ ፡
  • በቁጥጥር ስር መዋልዎ አስፈላጊ ካልሆነ መፈታት አለብዎት። ፖሊሶች የወንጀል ምርመራውን መቀጠል ከፈለጉ በዋስመ ሊለቀቁ ይችላሉ።
  • ፖሊስ የእስር ጊዜዎት እንዲራዘም ፍርድ ቤቱን በሚጠይቅ ግዜ፡
    • ፖሊስ የእስር ጊዜዎት እንዲራዘም ፍርድ ቤቱን በሚጠይቅ ግዜ፡
    • ጉዳዩ በሚሰማ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ አለብዎት የሚል መግለጫ በጽሑፍ ሊሰጥዎት እንዲሁም ጽሑፉ ለምን ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ እስር ቤት የሚቆዩበት ለማራዘብ ብሎ ሊገልጥ ይገባል።
    • የቴሌቭዠን ግንኙነቱ ተሰናድቶ በፍርድ ቤት ያሉ ሰዎእን እየተመለከቱና እያዳመጡ እንዲሁም ሰዎቹምነተ እርሶን እየተመለከቱና እያዳመጡ ካልሆነ በስተቀር ወደ ፍርድ ቤት መምጣት ይኖርቦታል፡፡
    • ፍርድ ቤት ሲቀርቡም ጉዳይዎ ሊታይሎት ጠበቃ አብሮዎ እንዲም መብት አለዎት።  ፖሊሶች በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ የሚፈቀደው ፍርድቤቱ አስፈላጊነቱን ሲያምን እና ፖሊሶች ጉዳዩን በጥንቃቄ እየመረመሩ እንደሆነ እና ግዜ እንደማያጠፉ ካመነ ብቻ ነው።
  • ፖሊሶች ፍርድ ቤት ለማቅረብ በቂ መረጃ ካላቸው ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ እያሉ ወይም በደብዳቤ ክስ ይመሰረትብዎ እና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡና እንዲፈረድብዎ ይሆናል።

ምርመራ እና የሚታሰሩበት ጊዜ ማራዘም

  • ከታሰሩ በኋላ ከ 48 ሰአታት በላይ እስር ቤት ሊቆይ የሚችሉበት አንዳንድ እጋጣሚዎች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ካጋጠሙ፣ የሚቀጥሉት ነገሮች ሊሰጦች ይገባል፡-
    • እስር ቤት የሚቆዩበት ጊዜ እንዲራዘም ማመልከቻ እንደቀረበላችሁ የሚያሳይ ጽሑፍ መግለጫ፣
    • ማመልከቻው የቀረበበት ጊዜ፣
    • የቀረበው ማመልከቻ በፍርድ ቤት ውስጥ የሚያይበት ጊዜ፣ እና
    • ለተጨማሪ ጊዜ እስር ቤት እንዲቆዩ ማመልከቻ የቀረበበት ምክንያት(ቶች)።

ለእርስዎ እና ለየሕግ አማካሪዎ እስር ቤት የሚቆይበት ጊዜ ለማራዘም ማመልከቻ በቀረበበት ሰዓት መረጃ ሊሰጣችሁ ይገባል።

11. ጉዳዮ ፍርድ ቤት ሲቀርብ መረጃ የማየት ፍቃድ

  • ባጥፊነት ክስ ከተመሰረተብዎት እርስዎ እና ጠበቃዎ የቀረበብዎን መረጃ እና ለመከራከሪያ የሚረዳዎትን መረጃ እንድታዩ ሊፈቀድላችሁ ይገባል። ይህም ጉዳዩ ፍርድቤት ከመታየቱ በፊት መደረግ አለበት። ፖሊሶችና አቃቤሕግ እነኚህን መረጃዎች እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እንዲያዩና እንዲያገኙ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።

ፖሊስ ጣቢያ እያላችሁ ማወቅ የሚገባችሁ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች።

ሊደረግልዎ ስለሚገባ አያያዝና እንክብካቤ

እነዚህ ፅሁፎች በፖሊስ ጣቢያ በሚቆዩበት ወቅት ምን ሊጠብቁ እንደሚገባ የሚገልጹ እርስዎን ለማሳወቅ የሚችሉ መረጃዎች ናቸዉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የፖሊስ አሰራር ደንቡን ይመልከቱ፡፡ ፅሁፎቹ ከታች ስለተገለፁ ነገሮች ተጨማሪ መረጃ የት እንደሚያገኙ የሚገልፁ ናቸዉ፡፡ ጥያቄ ካለዎ የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑን ያነጋግሩት፡፡

እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች

  • እድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ፣ ትምህርት የመቀበል ችግር ካለብዎ በቀላሉ በአደጋ ሊወድቁ የሚችሉ ከሆነወይም የአእምሮ ጤና ችግር ካለብዎ ፖሊሶች ስራቸዉን ሲሰሩ ከጎንዎ ሰው እንዲኖር የማድረግ መብት አለዎት፡፡ ይህም ሰዉ ‹‹ተገቢነት ያለዉ አዋቂ ሰዉ›› ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የዚሁ ግልባጭ መግለጫ ይሰጦታል።
  • ፖሊሶች ስለመብትዎና ለምን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሲነግርዎ የርስዎ ተገቢው አዋቂ ሰዉ አብርዎት ሊሆን አለበት፡፡ ሁሉንም ነገር በግልጽ እንደተረዳችሁት ሊያረጋግጡ ይችላሉ። የፖሊስ ጥንቃቄ በሚነበብልዎት ጊዜም ይህ ሰዉ አብሮዎት መሆን ይገባዋል፡፡
  • ተገቢው አዋቂ ሰው ርስዎን በመወከል የሕግ አማካሪዎን ሊያነጋግረልዎ ይችላል፡፡
  • የሚፈልጉም ከሆነ ተገቢዉ አዋቂ ሰዉ ክፍልዎ ዉስጥ በሌለበት የሕግ አማካሪዎን ማነጋገር ይችላሉ፡፡
  • ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ባሉበት ወቅት ፖሊስ ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ለማድረግ ይፈልግ ይሆናል፡ ልዩ ምክንያት ከሌለዉ በስተቀር ፖሊስ የሚከተሉትን ነገሮች በሚያደርጉበተ ወቅት ተገቢነት ያለዉ አዋቂ ሰዉ አብርዎት ሊኖር ይገባል፡፡
    • ቃለመጠይቅ ሲያደጉዎት ወይም የፅሁፍ መግለጫ ወይም የፖሊስ ማስታወሻ እንዲፈረሙ ሲጠይቅዎት፤
    • ከላይ ከለበሱት ውጪ ለፍተኛ ልብሶን እንዲያወልቁ ከጠየቁዎት፤
    • አሻራዎ ፎቶግራፍዎ ወይም ዲኤንኤ ወይም ሌላ ናሙና ይወሰዳል።
    • ኤላ ተጨማሪ አስፈላጊ የሆነ ምርመራስለ ተጨማሪየአይነምስክር መለያ አገባብ አሰራር መንገድ።
  • ፖሊስ ለተጨማሪ ግዜ መታሰር እንዳለቦት ለማወቅ ጉዳዮትን በሚተመግም ግዜ የእርሶ ተገቢ አዋቂ ሰው በአካል ወይም በስልክ በመገኘት ለማገዝ እድል መስጠት አለበት፡፡ እየጠበቁ መሆናቸው እና በጥፋተኝነት ክስ በሚያቀርቡብዎ ግዜ መገኘት አለባቸው።
  • የእርስዎ ተገቢ አዋቂ ሰው ፖሊስ ክስ ሲያቀርብሎት እዛ ከእርስዎ ጋር አብሮው መገኘት አልባቸው።

በፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ስለመቆየት ሊያዉቋቸዉ የሚገቡ ሌሎች ነገሮች የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ ጊዜዎን ዝርዝር ማግኘት

  • በፖሊስ ጣቢያ ቆይታዎ ላይ የሚሆን ማንኛዉም ነገር ይመዘገባል፡፡ ይህ የጥበቃ መዝገብ ይባላል፡፡
  • ከፖሊስ ጣቢያዉ ሲወጡ ርስዎ፣ የርስዎ የሕግ አማካሪ ወይም ተገቢ የሆነ አዋቂ ሰዉ የጥበቃ መዝገቡን ግልባጭ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ፖሊሶች የጥበቃ መዝገቡን በተቻለ ፍጥነት ሊሰጥዎ ይገባል፡፡
  • የጥበቃ መዝገቡን ግልባጭ ከፖሊስ ጣቢያዉ ከወጡ እስከ 12 ወራት ድረስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ለቀጣይ ግኑኘት

  • አብዛኛዉን ጊዜ የሕግ አማካሪ ለማነጋገርም ይሁን መታሰርዎን ለሌላ ሰዎች ለማሳወቅ ሲፈልጉ አንድ የስልክ ጥሪ እንዲያደርጉ ይፈቀድልዎታል፡፡
  • ስልክ የሚፈልጉ ከሆነ ለፖሊስ ያሳዉቁ፡፡
  • እስክሪብቶና ወረቀትም ከፈለጉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ሰዎች በእስር እንዳሉ ሊጎበኙዎት የሚችሉ ቢሆንም ይህንን ግን የፖሊስ ጥበቃ መኮንኑ ሊከለክል ይችላል፡፡

የእስር ክፍልዎ

  • የሚቻል ከሆነ ብቻዎ በራስዎ ክፍል ብቻ መሆን ይኖርቦታል፡፡
  • ንጹህ፣ ሞቃትና ብርሀናማ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • መኝታዎ ንጹህና የተሰናዳ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • መፀዳጃ ቤትና የመታጠቢያ አገልግሎትም ሊያገኙ ይገባል፡፡

አልባሳት

የግል አልባሳትዎ ከተወሰደብዎት ምትክ አልባሳት ፖሊስ ሊሰጥዎ ይገባል፡፡

ምግብና መጠጥ

በቀን ሶስት ጊዜ ምግብ ከመጠጥ ጋር ሊቀርብልዎ ይገባል፡፡ ከምግብ ሰአት ዉጭም የሚጠጣ ነገር ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰዉነት እንቅስቃሴ

የሚቻል ከሆነ በየቀኑ ደጅ ወጥተው እንዲናፈሱና ንጹህ አየር እንዲያገኙ ሊፈቀድልዎ ይገባል፡፡

በፖሊስ ምርመራ ወቅት፡-

  • ክፍሉ ንፁህ፣ በቂ ሙቀትና ብርሃን ያለበት ሊሆን ይገባል፡፡
  • ሊቆሙ አይገባም፡፡
  • መርማሪ ፖሊሶቹ ስማቸዉንና ማዕረጋቸዉን ሊነግርዎት ይገባል፡፡
  • በተለመደዉ የመመገቢያ ሰአት እና በየሁለት ሰአቱ የሚጠጣ ነገር ለመዉሰድ የእረፍት ጊዜ ሊሰጥዎት ይገባል፡፡
  • በፖሊስ ጥበቃ ዉስጥ ሲቆዩ በ24 ሰዓት ዉስጥ በትንሹ 8 ሰዓት እንዲያርፉ ሊፈቀድልዎ ይገባል፡፡

የእምነት ጉዳዮች

  • ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እያሉ እምነትዎን ለማምለክ የሚያስፈልጉዎ ነገሮች ካሉ ለፖሊሶች ይናገሩ።የሃይማኖት መጽሐፍትና ሌሎችም እቃዎችን በማቅረብ ሊረዱዎ ይችላሉ።

የተለመዱ ሕጎች የሚቀየሩበት ጊዜያት

የሚረዳዎ የሕግ አማካሪ ማግኘት

የሕግ አማካሪዎን ከማግኘትዎ በፊት ፖሊስ በአስቸኳይ ጥያቄ ሊጠይቅዎ የሚፈልግበት አንዳንድ ልዩ አጋጣሚዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለነዚህ ልዩ ሁኔታዎች መረጃ በአሰራር ደንቡ ዉስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡ ይህ መጽሐፍ በፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ፖሊስ ምን ማድረግና አለማድረግ እንዳለበት የሚያስቀምጥ ነዉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡ ክፍል ሸ (H) አንቀፅ 6.7 ዉስጥ ተካቶ ይገኛል።

ፖሊስ የመረጡትን የሕግ አማካሪዎትን እንዳያነጋግሩ ሊከለክልዎት የሚችልበት አንድ ልዩ ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ሌላ አማካሪ እንዲመርጡ ሊፈቅድልዎ ይገባል፡፡ ዝርዝሩን መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡን ክፍል በ አነክስ ለ በ ኮድ ኦፍ ፕራክቲስ ሸ (Annex B Code H of Codes practice) ይመልከቱ አባሪ ቢን ይመልከቱ፡፡

ፖሊስ የመረጡትን የሕግ አማካሪዎትን በግል እንዳያነጋግሩ ሊከለክልዎት የሚችልበት አንድ ልዩ ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ደግሞ የፖሊሶች ዋና ሐላፊ ለዩኒፎርም የሚለብስ ፖሊስ ጠበቃው እና እርስዎ የሚነጋገሩት እንዲሰማ ቆሞ እንዲገኝ ሲያዝዝ ነው። ይህ አጋጣሚ መቸ እንደሚሆን ማወቅ ከፈለጉ ስለዚሁ ዝርዝር የሚገልጥ በ የአሰራር ደንቡ ክፍል ሸ (H) አንቀፅ 6.5 ዉስጥ ተካቶ ይገኛል።

ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ለሌሎች ስለማሳወቅ

ፖሊስ ከማንም ሰዉ ጋር እንዳይገናኙ ሊከለክልዎ የሚችልበት ልዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ልዩ ሁኔታዎች በአሰራር ደንቡ ዉስጥ ተካተዉ ይገኛሉ፡፡ ዝርዝሩን መመልከት ከፈለጉ የአሰራር ደንቡን ዝርዝር በ Annex B Code H of Codes practice አነክስ ለ በ ኮድ ኦፍ ፕራክቲስ ሸ (Annex B Code H of Codes practice) ላይ አሉ፡፡

ነፃ እስረኛ ጎብኝዎች

በድንገት ፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ በመገኘት እስረኞችን እንዲጎበኙ የተፈቀደላቸዉ ነፃ የእስረኛ ጎብኝዎች የተባሉ በጎ ፈቃደኛ የማህበረሰብ አባላት አሉ፡፡ ስራቸዉም እስረኞች በአግባቡ መያዛቸዉንና መብቶቻቸዉ የተጠበቁላቸዉ መሆኑን ማረጋገጥ ነዉ፡፡

ነፃ እስረኛ ጎብኝዎች ጋር ልገናኝ ወይም መጥተዉ ይጎብኙኝ ብለዉ የመጠየቅ መብት የለዎትም፡፡ ነገር ግን በፖሊስ ጥበቃ ስር እያሉ ጎብኝዎቹ እርስዎን የመጎብኘት አጋጣሚ ካገኙ ከፖሊስ ተፅዕኖ ነፃ በሆነ ሁኔታ የእርስዎ ደህንነትና መብትዎ መጠበቁን ያረጋግጣሉ፡፡ ማጋገር ካልፈለጉ አለማነጋገር ይችላሉ፡፡

ቅሬታን እንዴት ማቅረብ ይቻላል

ስለተደረገልዎ አያያዝ ቅሬታ ለማቅረብ ከፈለጉ፣ መርማሪ ፖሊሱን ወይም ከፍ ያለ ማዕረግ ያለዉን ፖሊስ ለማነጋገር ይጠይቁ፡፡ ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ቅሬታዎን ማቅረብ ቢፈልጉ ለነፃ የፖሊስ ቅሬታ ሰሚ ኮሚሽን ወይም ኦፊስ ፎር ፖሊስ (Office for Police Conduct (IOPC)) ኮንዳክት በሕግ አማካሪዎ በኩል ወይም MP የፖርላማ አባልዎ አማካኝነት መጠየቅ ይችላሉ።